ሐምሌ 18 2017
ኢትዮጵያ ከውጪ ለምታስገባቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከወደብ ወደ መሀል ከተማ በባቡር የማጓጓዝ አገልግሎት ጀመረች ተባለ።
ይህንን ስራ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ያቀላጥፈዋል መባሉን ሰምተናል።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የተሽከርካሪ አስመጭዎች እና የሚመለከታቸው ሁሉ በዚህ መንገድ እንዲያልፋ ምድር ባቡሩ መደላድሎችን ፈጥሯል ተብሏል።
በተለይ እነዚህን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከወደብ ወደ መሀል ሀገር ለማጓጓዝ የነበረውን ድካም እንደሚያስቀር የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ነግሮናል።
Comments