በሰሜን ወሎ ዞን የቡግና ወረዳ ነዋሪ የምግብ ድጋፍ ካገኙ ከሀያ ቀን በላይ ሆኗቸዋል ተባለ
TRACK

በሰሜን ወሎ ዞን የቡግና ወረዳ ነዋሪ የምግብ ድጋፍ ካገኙ ከሀያ ቀን በላይ ሆኗቸዋል ተባለ

Avatar

መጋቢት 4 2017

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቡግና ወረዳ ነዋሪ የምግብ ድጋፍ ካገኙ ከሀያ ቀን በላይ ሆኗቸዋል ተባለ፡፡

ከወራት በፊት በዞኑ ረሀብ ጠንቶ መክረሙን በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲነገር መቆየቱን ተከትሎ መንግስትም፣ ህዝቡም ሆነ ረጅ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረግ እንደጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ነገር ግን ከሀያ ቀናት በፊት በመንግስትም ሆነ በረጅ ድርጅቶች ይደረግ የነበረው ድጋፍ መቋረጡን የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ነግሮናል፡፡

ባለፈው የክረምት ወቅት ባጋጠመ የዝናብ እጥረት የምርት አቅርቦት ችግር እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል በዚህም ደግሞ ነዋሪው ለምግብ እጥረት ተጋልጧል፡፡

Comments

Avatar