00:00
ሐምሌ 18፣ 2016
በተለያየ ምክንያት ፈቃዳቸው የተሰረዙ የ1700 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ሃብትና ንብረት አጣርቶ ተመሳሳይ አላማ ላላቸው ሌሎች ድርጅቶች ለማስተላለፍ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ህልውናቸውን ያላረጋገጡና የተሻሻለውን አዋጅ ተከትሎ ዳግም ምዝገባ ያላደረጉ ድርጅቶችን ፍቃድ መሰረዙን ተናግሯል።
ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ህልውናቸውን አላረጋገጡም በሚል የሰረዛቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን እና የስራ ክንውናቸውን የተመለከተ ሪፖርት ያላቀረቡ ናቸው ተብሏል።
እነዚህ ቁጥራቸው 205 እንደሆነ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ነግረውናል።
Comments
00:00