የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰንበት ካማሺ ዞን ከሰሞኑ በተፈፀመ ጥቃት ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ
TRACK

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰንበት ካማሺ ዞን ከሰሞኑ በተፈፀመ ጥቃት ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ

Avatar

ሚያዝያ 2 2017

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰንበት ካማሺ ዞን ከሰሞኑ በተፈፀመ ጥቃት ከ1 ሺህ 500 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተሰማ፡፡

በስጋትም ምክንያት የተፈናቀሉ አሉ የተባለ ሲሆን አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች መጠለላቸውን ሰምተናል፡፡

የኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚዋሰኑበት አካባቢ ነዋሪ የነበሩ 1,500 ሰዎች ባለፈው ሳምንት ሸኔ አድርሶባቸዋል በተባለ ጥቃት እና በስጋት ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል ተባለ፡፡

ተፈናቃዮቹ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚቺጋ ወረዳ ነዋሪዎች እንደሆኑ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር መሃመድ አብንዱልአዚዝ ነግረውናል::

Comments

Avatar