ሰኔ 24 2017
የመንግስት የወጪ ፍላጎት በገቢ አቅሙ መሸፈን አለበት የሚል ጠንካራ አቋም መያዙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ በ2018 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ዙሪያ ዛሬ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
የ2018 የፌዴራል መንግስት ጠቅላላ ወጪ በጀት 1.93 ትሪሊየን ብር ሆኖ መዘጋጀቱ ይታወሳል።
ከተያዘው አጠቃላይ በጀት 1.2 ትሪሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 415.2 ቢሊየን ብር ለካፒታል ወጪ፣ 315 ቢሊየን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍ እና 14 ቢሊየን ብር ለክልሎች የዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የተደለደለ እንደሆነ ተነግሯል።
ለአመቱ ከተያዘው 1.93 ትሪሊየን ብር ውስጥ 1.23 ትሪሊየን ብር ታክስ እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ይሰበሰባል ተብሎ ግብ ተቀምጧል።
ለዓመቱ በተዘጋጀው ረቂቅ በጀት ዙሪያ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።
የምክር ቤቱ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎችን በረቂቅ በጀቱ ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት ለተገኙት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ አቅርበዋል።
Comments