00:00
የካቲት 25/2018
አሁን ላይ ሁሉም ክልሎች ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ አዘጋጅተው ጨርሰዋል ተባለ።
በተለያየ ምክንያት አዋጁን የማዘጋጀቱ ስራ በክልሎች ተጓቶ እንደቆየ የፌዴራል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ተናግሯል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በፌዴራል ደረጃ መሻሻሉን ተከትሎ ክልሎችም ተመሳሳይ ማዕቀፍ ያለው ህግ ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተጠቅሶ በዚሁ ላይ ሲሰራ መቆየቱ ተነግሯል።
ክልሎች ተመሳሳይ ይዘት ያለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ማውጣት አለባቸው የተባለው የፌዴራሉ አዋጅ ተፈጻሚነት በፌዴራል በሚመዘገቡት ላይ ብቻ ስለሆነ ነው ተብሏል።
Comments
00:00