የካቲት 10/2018
አንዳንድ የጸጥታ ችግር ባሉባቸው አካባቢዎችና የጤና አገልግሎት መስጫ ባልተስፋፋቸው ቦታዎች የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት በሚፈለገው ልክ እየተተገበረ አይደለም ተባለ፡፡
ከጸጥታ ስጋቱ በተጨማሪ ስለአገልግሎቱ የሚሰጡ የተሳሳቱ አስተያየቶችም ችግር መሆኑ ተነግሯል፡፡
የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት መጠቀም ቢፈልጉም በተለያየ ምክንያት ዕክል የገጠማቸው አፍላ ወጣቶች ላይ በማተኮር አገልግሎቱ እንዲስፋፋ እያደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በቅርቡ በተከወነ ጥናት በሀገሪቱ የውልደት ምጣኔው መቀነሱ የተነገረ ቢሆንም አሁንም ግን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቱን ማስፋፋት ላይ የሚቀሩ ስራዎች አሉ የሚሉት በጤና ሚኒስቴር የስነ ተዋልዶ ጤና የቤተሰብ ዕቅድና የወጣቶች ፕሮግራም ሀላፊ የሆኑት ዶክተር አለማየሁ ሁንዱማ ናቸው፡፡
Comments