00:00
የካቲት 26/2018
በተለያዩ አካባቢዎች ባለ የሰላም እጦት እና የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ለመደገፍ የሚያስችል ሁለተኛ ዙር ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባቱ ተነገረ፡፡
በአለም ባንክ የሚደገፈው እና ለአምስት አመታት ይቆያል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ሊጠናቀቅ ሁለት አመታት እንደቀረው ሲነገር ሰምተናል፡፡
በዚህም ሁለተኛው ምዕራፍ እና በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ይተገበራል የተባለው ስራ ወደ ትግበራ መግባቱ ተነግሯል፡፡
በጦርነት ምክንያት ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የጤና ድጋፍ እንዲያገኙ፣ የኢኮኖሚ ምስቅልቅል የገጠማቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮቻቸው ላይ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑ ተነግሮለታል፡፡
Comments
00:00