ጥቅምት 18 2018
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመታት ፀብ በኋላ መልሰው ሰላም ባወረዱ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጥረት የገቡት በቀይ ባህር ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ፡፡
ውጥረቱ ወደ አደባባይ የወጣው ግን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በእርቁ ሰሞን በሁለቱ ሃገራት መካከል ድንበሮች ተከፍተው፣ የአሰብን ወደብም ኢትዮጵያ ልትጠቀም ሂደት ተጀምሮ እንደነበር በማስታወስ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከፓርላማ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ በመሰጡት ምላሽ ነው፡፡
የቀይ ባህር ጉዳይ መልክአ ምድራዊ እና ታሪካዊ ጥያቄ በመሆኑ በሰከነ መንገድ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን የባህ በር ያሳጣትን ታሪካዊ ዳራ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈንደም ያልተወሰነበት ፓርላማው የማያውቀው፣ የካቢኔ ውሳኔም ያልተላለፈበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
Comments