ግንቦት 8 2017
ኢትዮጵያ የተዘረፉ ቅርሶቿን ጨረታ ላይ ሲወጡ ጭምር እየገዛች ለማስመለስ ተገዳለች ተባለ፡፡
ቅርሶች በህገ-ወጥ መንገድ ሲወጡ የኢትዮጵያ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ሰነድ ስለማይኖር ለማስመለስ ካሳ ትጠየቃለች ተብሏል፡፡
በዘረፋ መልክ በህገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ቅርሶች በኢንተርፖል ስለማይመዘገቡ አሁን ላይ እየተመለሱ ካሉ ቅርሶች መካከል ገንዘብ ተከፍሎባቸው የመጡ ይገኙበታልም ተብሏል።
አንዳንድ ሀገራት ቅርስን የማስመለስ ህጋቸው ጥብቅ በመሆኑ በሙዚየማቸው ያሉ ቅርሶችን ለማስመለስም አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ሰምተናል።
Comments