TRACK
መድሀኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች ከግምጃ ቤት ጀምሮ እስከ ስርጭት ድረስ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግበት የሚያስችል የዲጅታል ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑ ተሰማ
መስከረም 9 2018
መድሀኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች ከግምጃ ቤት ጀምሮ እስከ ስርጭት ድረስ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግበት የሚያስችል የዲጅታል ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑ ተሰማ።
በኢትዮጵያ በሁሉም ክፍሎች መድኃኒቶችንና የህክምና ቁሳቁሶችን የመግዛት፤ የማከማቸት እና የማከፋፈል ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ይህ መንገድ የስራዬን ትክክለኝነት ያረጋግጥልኛል ብሏል።
በኢትዮጵያ የመድኃኒት ቁጥጥር እንዲሻሻል እና ከፍተኛ ሐብት የወጣበት ሐብት ቆጠራ ሥርዓት ትክክለኛነት እንዲረጋገጥ ይህ የዲጂታል መንገድ እንደሚያግዝ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ስማርት የዲጂታል ጤና አቅርቦትና ሰንሰለት ለመዘርጋት ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ውል ማሰራቸውን ሰምተናል።
Comments