ኢትዮጵያን ከውጭ ምንዛሪ ወጭ አድኗል የተባለው የጃፓን ኩባንያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ጀምሯል
TRACK

ኢትዮጵያን ከውጭ ምንዛሪ ወጭ አድኗል የተባለው የጃፓን ኩባንያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ጀምሯል

Avatar

ሰኔ 24 2017

ከዚህ ቀደም ከውጭ ይታተሙ የነበሩ እንደ ቼክ እና ፓስፖርት ያሉ ሚስጥራዊ ህትመቶችን በሀገር ቤት ለማተም፤ ኢትዮጵያን ከውጭ ምንዛሪ ወጭ አድኗል የተባለው የጃፓን ኩባንያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ጀምሯል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮ ልማት ኮርፖሬሽን ሌሎችም የጃፓን ኩባንያዎች በተለይም በመድሃኒት ማምረች ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ እያቀረብኩ ነው ብሏል፡፡

የጃፓን ባለሃብቶች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ምንም ተሳትፎ አልነበራቸውም።

በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ገብቶ ለመስራት የመጀመሪያ የሆነው የጃፓን ኩባንያ ቶፓን ግራቪቲ እንደሚሰኝ ሠምተናል።

ከአንድ አመት በፊት ስራ የጀመረው ቶፓን ግራቪቲ እንደ ፓስፖርት እና ቼክ ያሉ ሚስጥራዊ ህትመቶች ላይ እየሰራ እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ እንድታድን እያገዘ ነው ሲሉ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፤ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ተናግረዋል።

Comments

Avatar