በኢትዮጵያ የዓለም የጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠው አንድ በመቶ የለጋሾች ቁጥር እስካሁን የተገኘው ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ ያህል መሆኑን ሰምተናል
TRACK

በኢትዮጵያ የዓለም የጤና ድርጅት ከሚያስቀምጠው አንድ በመቶ የለጋሾች ቁጥር እስካሁን የተገኘው ዜሮ ነጥብ አምስት በመቶ ያህል መሆኑን ሰምተናል

Avatar

ሰኔ 9 2017

በተለያዩ አደጋዎች በወሊድ ጊዜ እንዲሁም ሌሎች የደም ፍላጎትን ለሚጠይቁ የህክምና ስራዎች የሚውል ደም ከበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች በሚገኝ አቅርቦት ነው የሚሟላው፡፡

በኢትዮጵያ በየጊዜው ለዚሁ አላማ በተለያዩ ተቋማት ግለሰቦችና በጎ ፈቃደኞች ደም ይለገሳል፤ ነገር ግን አሁንም ፍላጎቱ ከአቅርቦቱ ጋር አልተጣጣመም፤ ይህንንም ለማሟላት የተለያዩ የግንዛቤና የማሳወቅ ስራዎችም ይሰራሉ፡፡

የደም ልገሳ በኢትዮጵያ ከተጀመረ ከ50 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩ ይነገራል።

በእነዚህ ዓመታት ውስጥም በጎ ፈቃደኞች በለገሱት ደም የብዙዎች ህይወት ቀጥሏል፣ ከሞትም መታደግ ተችሏል፡፡

እነዚህ ልበ ቀና በጎፈቃደኛ ደም ለጋሾዎች የሚታሰቡበት ቀንም በኢትዮጵያ ተከብሯል፡፡

ቀኑ የሚከበረው ደም ለጋሾችን ለማመስገን የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ የብዙዎችን ህይወት ለማዳን ያለውን አስተዋጾ ለማሳየት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ለመሆኑ አንድ ሰው እስከ ምን ያህል ጊዜ ደም ይለግሳል? ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ በኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ ባለሙያ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በጎ ፈቃድ ደም ለጋሽ።

እርሳቸው ለ 120 ጊዜ በበጎ ፈቃደኝነት ደም በመለገስ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፤ አሁንም ለ121ኛ ጊዜ ደም ለግሰዋል፡፡

Comments

Avatar