ታህሳስ 24፣2017
ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተግብራለች፡፡
ከቅርቡ የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያ እስከ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ድረስ፡፡
እነዚህ ማሻሻያዎች የሀገሪቱን ገቢ ለማሳደግ የሰዎችን ሕይወት ለመለወጥ እንዲሁም የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ማሻሻያዎቹ እንደሚረዱ ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማህበር ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ናሲር የኑስ (ዶ/ር) የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚም ሆኑ ሌሎች ማሻሻያዎች ለሀገሪቱ ጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ይሁንና የተደረጉት ማሻሻያዎች ፍሬ ማፍራት የሚችሉት ወደ መሬት ወርደው መተግበር ሲችሉ ነው ይላሉ፡፡
Comments