TRACK
ባለፈው ሳምንት ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማፅደቋ ስምምነቱ አለም አቀፍ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ ያስችላል ተባለ፡፡
ሐምሌ 11፣ 2016
ባለፈው ሳምንት ደቡብ ሱዳን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ማፅደቋ ስምምነቱ አለም አቀፍ ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ ያስችላል ተባለ፡፡
ከ14 ዓመታት በላይ በድርድር ላይ የቆየው የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ (The Nile Basin Cooperative Framework Agreement) ህግ ሆኖ እንዲፀድቅ የሚያስችለውን ይሁንታ ከደቡብ ሱዳን አግኝቷል፡፡
ይህ ስምምነት ለኢትዮጵያ ምን ያስገኛል ያልናቸው የአባይ ጉዳይ ውሃ ጉዳይ ተመራማሪ የሆኑት ፈቅ አህመድ ነጋሽ፤ የደቡብ ሱዳን ስምምነቱን ማፅደቅ ትብብሩን ያፀደቁ የአገራቱን ቁጥር ወደ 6 ከፍ ያደርገዋል ይህም በአለም አቀፍ ደረጃ ህግ ሆኖ ለመፅደቅ ያስችለዋል ይላሉ፡፡
ይህ ስምምነት መፅደቁ በዋናነት ለኢትዮጵያ የሚኖረው ጥቅም ምንድነው? ከተባለ ትልቁና የመጀመሪያው ጥቅም ከአሁን በፊት በተፋሰሱ ውስጥ አገልግሎት ላይ የነበረውን የቅኝ ግዛትና ደህረ ቅኝ ግዛት ስምምነቶች ማለትም የ1929 እና የ1959ኙ ስምምነት በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋ እንዲያጡ የሚያደርግ ነው ብለዋል ተመራማሪው፡፡
Comments