ኢትዮጵያ ዘንድሮ በታሪኳ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ወደ ውጪ ከተላከ ቡና ማግኘቷ ተነገረ
TRACK

ኢትዮጵያ ዘንድሮ በታሪኳ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ወደ ውጪ ከተላከ ቡና ማግኘቷ ተነገረ

00:00

ሐምሌ 2፣ 2016

ኢትዮጵያ ዘንድሮ በታሪኳ ከፍተኛ የሆነ ገቢ ወደ ውጪ ከተላከ ቡና ማግኘቷ ተነገረ።

በዓመቱ ወደ ተለያዩ አገራት ከተላከ 298 ሺህ 500 ቶን ቡና 1 ነጥብ 43 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል ተብሏል።

ዘንድሮ ወደ ተለያዩ ሀገራት ከተላከ ቡና ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷ ተነግሯል።

ገቢው ከዚህ ቀደም ተገኝቶ የማያውቅ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሰልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር) ነግረውናል።

ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ገቢ ወደ ውጪ ከተላከ ቡና የተገኘው ከሁለት ዓመት በፊት እንደነበር ያስታወሱት ዳይሬክተሩ የዘንድሮው ግን ከዚያም የበለጠ ሆኗል ብለዋል፡፡

Comments

00:00