በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ከ26,000 ሊትር በላይ ነዳጅ ተወረሰ
TRACK

በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ከ26,000 ሊትር በላይ ነዳጅ ተወረሰ

Avatar

ታህሳስ 24፣2017

በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጥ የነበረ ከ26,000 ሊትር በላይ ነዳጅ ተወረሰ፡፡

ነዳጁን ሲሸጡ የተያዙት ማደያዎችና ግለሰቦች ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ የተወረሰው ነዳጅም በህጋዊው ገበያ ተሽጦ ከ2.4 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ መንግስት ካዝና ገብቷል ተብሏል፡፡

ይህ ገቢ የተገኘው በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች በህግ ከተፈቀደው ውጪ በጄሪካን እየተቀዳ ከተተመነው ዋጋ በላይና ያለ ኤሌክትሮኒክስ መላ ሲሸጥ መሆኑን ተቆጣጣሪው አካል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነግሮናል፡፡

ቢሮው ህገወጥ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠር ይረዳኛል፣ የማህበረሰቡንም እንግልት ይቀንሳል ብሎ ከሁለት ወራት በፊት በጀመረው ማደያዎችን በቀን ሁለት ጊዜ የመቆጣጠር ስራ በዚህ ተግባር ውስጥ ተገኝተዋል ያላቸውን 9 ማደያዎች ሲሸጡት የነበረውን ነዳጅ ወርሰን አሽገናቸዋል ብሏል፡፡

Comments

Avatar