ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ሲያመርቱ ነበር የተባሉ 52 ፋብሪካዎች እንዳይሰሩ መታገዳቸው ተነገረ
TRACK

ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ሲያመርቱ ነበር የተባሉ 52 ፋብሪካዎች እንዳይሰሩ መታገዳቸው ተነገረ

Avatar

ሐምሌ 10 2017

ከደረጃ በታች የሆነ ምርት ሲያመርቱ ነበር የተባሉ 52 ፋብሪካዎች እንዳይሰሩ መታገዳቸው ተነገረ።

ፋብሪካዎቹ ታሽገው ያሰራጩትን ምርት ከገበያ እንዲሰበስቡ መደረጉን ሸገር ኤፍ ኤም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሠምቷል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ412 ፋብሪካዎች ላይ የምርት ጥራት ቁጥጥር ማካሄዱን ጠቅሷል።

ከእነዚህ 412 ፋብሪካዎች ከ152ቱ ላይ 236 ወካይ ናሙና በመውሰድ የምርት ጥራት ምርመራ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ድኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ነግረውናል።

ከ152ቱ ፋብሪካዎች መቶዎቹ የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ ጠብቀው እያመረቱ ስለመሆናቸው በቁጥጥሩ ወቅት ተረጋግጧል ብለዋል።

Comments

Avatar