ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል እያቀረበች ያለችው ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ለደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገች ነው ተባለ
TRACK

ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል እያቀረበች ያለችው ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ለደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገች ነው ተባለ

Avatar

ጥር 25/2018

ለኬንያ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል እያቀረበች ያለችው ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ ለደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገች ነው ተባለ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት አቅም 9750 ሜጋ ዋት፤እየመነጨ ያለው ደግሞ 9730 ሜጋ ዋት መሆኑ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ሲናገሩ እንደሰማነው በኢትዮጵያ ከስድስት አመት በፊት የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም በእጥፍ አድጓል።

4 ሺህ ሜጋ ዋት ገደማ የነበረው ከታዳሽ የሀይል ምንጭ የኤሌክትሪክ ሀይል የማመንጨት አቅም አሁን 9750 ሜጋ ዋት መድረሱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት እየመነጨ ካለው ኃይል 9200 ሜጋ ዋቱ ከውሃ፣ 550 ሜጋ ዋት ደግሞ ከንፋስ የሃይል ምንጭ የሚገኝ መሆኑም ተነግሯል።

ለሀይል መጠኑ መጨመር ትልቁ ድርሻ የህዳሴው ግድብ መጠናቀቅ መሆኑ ተነግሯል።

Comments

Avatar