TRACK
በ22 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርትና ጠቅላላ ምርቱ ለዜጎች የነብስ ወከፍ ሲሰላ ከ2016 ጀምሮ እየቀነሰ መምጣቱን ጥናት አሳይቷል
ግንቦት 14 2017
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ2001 እስከ 2023 ባለው 22 ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አፈፃፀምና አስተዳደር ምን ይመስላል? የሚል ጥናት አድርጓል፡፡
በ22 ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርት #GDP እና ጠቅላላ ምርቱ ለዜጎች የነብስ ወከፍ ሲሰላ ከ2016 ጀምሮ እየቀነሰ መምጣቱን ጥናቱ አሳይቷል፡፡
የዋጋ ግሽበት በእነዚህ ዓመታት ጨምሯል በዚህም ምክንያት የሃገሪቱ ማክሮ ኢኮኖሚው ሚዛኑን እንዳይጠብቅ አድርጎታል የዜጎች ገቢ እንዲቀንስ አድርጓል ኢንቨስትመንት ቀንሷል ተብሏል፡፡
እስከ 2019 ድረስ ባለው ዓመት የማምረት አቅም እያደገ የነበረ ሲሆን ከዛ በኋላ ግን የኢትዮጵያ የማምረት አቅም ባለበት እየሄደ መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና ምርት ለሀገራዊ ምርት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀንሷል ይህም የሆነው የሰርቪስ ዘርፉ እድገት እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡
በሀገሪቱ የማዳበሪያ አጠቃቀም ለአለም አቀፉ ደረጃ ከተቀመጠው ደረጃ ጋር ሲመሳከር ዝቅተኛ መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡
Comments