ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዲፖ እና ቢያንስ አምስት ማደያ እንዲኖራቸው በህግ ሊገደዱ ነው
TRACK

ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዲፖ እና ቢያንስ አምስት ማደያ እንዲኖራቸው በህግ ሊገደዱ ነው

Avatar

ህዳር 16፣2017

ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዲፖ እና ቢያንስ አምስት ማደያ እንዲኖራቸው በህግ ሊገደዱ ነው፡፡

ለፓርላማ ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት ውይይት እየተደረገበት ያለው የነዳጅና ነዳጅ ውጤቾች ግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ እንደሚለው ነባር የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች 5,000 ሊትር ክምችት የሚይዝ ዲፖና ለጊዜው ሶስት ማደያ እንዲኖራቸው ያስገድዳል፡፡

በ2 አመት ውስጥ ግን ተጨማሪ 2 ማደያ ገንብተው 5 እንዲያደረሱት ህጉ ተደንግጓል፡፡

ኩባንያው አዲስ ከሆነ ሲጀምር 2,500 ሊትር የሚይዝ ዲፖና ሁለት ማደያ ይዞ ስራውን መጀመር ይችላል የተባለ ሲሆን የተጠቀሰውን ደረጃ በ2 ዓመት ውስጥ እንዲያሟላ ህጉ ያስገድዳል፡፡

የነዳጅን ግብይትን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት፣ የሚታየውን ምርቱን የመደበቅና ከባዕድ ነገር ጋር የመቀላቀል ችግርም ለመፍታት ያግዛል የተባለው ይኸው ህግ በነዳጅ ግብይት ላይ ለመሳተፍ የብቃት ማረጋገጫ እንዲኖር የሚያስገድድ ነው ተብሏል፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ውይይት ሲደረግ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኙ ተወካይ አዋጅ በነዳጅ ማደያዎች የተለያየ ግዴታ መጣሉን ተናግረዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን ያሰባዳውን በፍቅሩ አምባቸው

Comments

Avatar