00:00
ሰኔ 4፣ 2016
መንግስት ካለበት የብድር እዳ ውስጥ 34 ከመቶ የሚሆነው የወሰዱት የልማት ድርጅቶች ናቸው ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር እዳ 65.77 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን 34 ከመቶ ወይም ወደ 22.36 ቢልየን ዶላር የሚያህለው እዳ የመንግስት የልማት ድርጅት ናቸው የያዙት ተብሏል፡፡
ይህ የተባለው የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተደራደር ረቂቅ አዋጅ ለማፅደቅ በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ግዢ ሥርዓት መሻሻል እንዳለበት ተነግሯል፡፡
Comments
00:00