በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በሚደርስ ስርቆት ከፍተኛ ሀብት እየባከነ ቢሆንም አጥፊዎችን በመቅጣት ረገድ ክፍተት መኖሩ ተሰማ
TRACK

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በሚደርስ ስርቆት ከፍተኛ ሀብት እየባከነ ቢሆንም አጥፊዎችን በመቅጣት ረገድ ክፍተት መኖሩ ተሰማ

00:00

መጋቢት 8 2017

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በሚደርስ ስርቆት ከፍተኛ ሀብት እየባከነ ቢሆንም አጥፊዎችን በመቅጣት ረገድ ክፍተት መኖሩ ተሰማ፡፡

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት ካለፉት ዓመታት አንፃር እየቀነሰ ቢሆንም ችግሩ ግን አሁንም በስፋት አለ የሚለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው፡፡

በመሰረተ ልማቶቹ ለላይ ጉዳት ያደረሰ ወይም ስርቆት የፈፀመ ማንኛውም ግለሰብ የእስር እና የገንዘብ ቅጣት የሚቀጣበት ህግ ቢኖርም ለፍርድ የሚቀርቡት ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል፡፡

በማህበረሰቡ በኩል ለተቋሙ የሚደርሱ ጥቆማዎችን በመከታተል ውሳኔ እንዲሰጥባቸው እናደርጋለን የሚሉት የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ ከሚደርሰው ጥፋት አንፃር ግን ወንጀሉን ፈፅመው በቁጥጥር ስር የማይውሉት ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም ብለውናል፡፡

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት የደረሰው ጉዳት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሀይልና የመሰረተ ልማት ስርቆት ተፈፅሟል ተብሏል፡፡

በዚህም በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት የኃይልና ሌሎች መሰረት-ልማት ሥርቆት ፈፅመው በፍርድ ቤት በተረጋገጠባቸው 11 የወንጀል ክሶች 13 ተከሳሾች ከሁለት ወር ቀላል እስራት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲፈረድባቸው ማድረግ ተችሏል ብለውናል፡፡

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ላይ 50 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መጣሉ የነገሩን ስራ አስፈፃሚው በሌሎች ተጠርጣሪዎች ክስ ተከፍቶ በክትትል ላይ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡

Comments

00:00