በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም ከ3,500 በላይ ሰዎች በፍርድ ቤት ፍቺ ፈፅመዋል ተባለ
TRACK

በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም ከ3,500 በላይ ሰዎች በፍርድ ቤት ፍቺ ፈፅመዋል ተባለ

00:00

ሐምሌ 17፣ 2016

በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም ከ3,500 በላይ ሰዎች በፍርድ ቤት ፍቺ ፈፅመዋል ተባለ፡፡

ቁጥሩ ከአምናው በ60 በመቶ ከፍ ማለቱን የሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ነው የተናገረው፡፡

በከተማዋ ከ90,000 በላይ ህፃናት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መወለዳቸውም ተሰምቷል፡፡

2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገበው የጋብቻ ቁጥር 18,215 ሲሆን ሞት 18,752 እንዲሁም ጉዲፈቻ 169 እንደተመዘገበ ሰምተናል፡፡

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ፍቺ እና ልደት ብልጫ እንዳላቸው ተነግሯል፡፡

Comments

00:00