ሐምሌ 10፣ 2016
በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመትን ዕቅዳቸውን አዘጋጅተው ሳይጨርሱ በልዩ ፍቃድ ግዥ ለመፈጸም እየጠየቁ ነው ተባለ።
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ግን ልዩ ፍቃድ የሚባል ነገር አይኖርም ብሏል።
የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ባለፈው ወር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል።
አዋጁ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ግዥ መፈጸም ያለባቸው በወረቀት አልባ ወይም ኤሌክትሮኒክ መላ ብቻ መሆን እንዳለበት ያዛል።
ግዢን ብቻ ሳይሆን የአመቱንም ዕቅድ ቀደም ብለው መስሪያ ቤቶቹ በኤሌክትሮኒክ መላ ማዘጋጀት እንዳለባቸው አዋጁ ይደነግጋል።
ይሁን እና በርካታ የመንግስት ባለ በጀት መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት አመትን ዕቅዳቸውን፤ አዘጋጅተው ሳይጨርሱ በልዩ ፍቃድ ግዥ ለመፈጸም እየጠየቁ ነው ተብሏል።
Comments