‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸዉ ዓይነ ስውራን የራሳቸው ምስክርነት እንደ ምስክርነት ባለመቆጠሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል’’
TRACK

‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸዉ ዓይነ ስውራን የራሳቸው ምስክርነት እንደ ምስክርነት ባለመቆጠሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል’’

Avatar

ታህሣስ 2፣2017

‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸዉ ዓይነ ስውራን የራሳቸው ምስክርነት እንደ ምስክርነት ባለመቆጠሩ ችግሩ እንዲባባስ አድርጎታል’’ ሲል የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማህበር ተናገረ።

ማህበሩ በአካል ጉዳተኛ ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጾታዊ ጥቃት በዓይነቱም በብዛትም እየጨመረ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ድባቤ ባጫ እንደ ማህበር ‘’ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸውን አካል ጉዳተኞች ፍትህ እንዲያገኙ እገዛ እያደረግን ነው ሆኖም ግን በተለይ ዓይነ ስውራን ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው ጥቃት ያደረሰባቸውን አካል በድምፅ በመለየት ምስክርነት እንዲሰጡ የሚያደርግ አሰራር ባለመኖሩ ፍትህ ለማግኘት ይቸገራሉ’’ ሲሉ ነግረውናል።

በሴት አካል ጉዳተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጾታዊ ጥቃት እንዲጨምር ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ ድህነት እና የግጭቶች መስፋፋት ተጠቃሽ መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ወ/ሮ ድባቤ ይናገራሉ።

Comments

Avatar