ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ
TRACK

ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ

Avatar

ጥቅምት 13፣2017

ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የ50ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከበረ።

ኤስኦኤስ የህጻናት መንደሮች(sos children village) በኢትዮጵያ ከተመሰረተበት1966 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ የሚሰራ የልማት ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በ50 ዓመታት ጉዞው በአጠቃላይ 8.1 ሚሊዮን ሰዎች በተለያዩ አገልግሎቶቹ መጥቀሙን ተናግሯል።

የእለት ደራሽ ድጋፍ ማቅረብ፣ የወጣቶች አቅም ግንባታና ጤና ድርጅቱ ከሚሰራቸው ስራቸው መካከል ይገኙበታል።

ኤስኦኤስ የህፃናት መንደር በ 50 ዓመት ውስጥ 100,000 ህፃናት ትምህርት እና ስልጠና አግኝተው ራሳቸውን እንዲችሉ አስረድቷል።

ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓትም 495,000 በላይ ሰዎች በተለያዩ ፕሮግራሞች አገልግሎት እየሰጠሁ ነው ብሏል።

Comments

Avatar