ከሰሞኑ ባንዳንድ የመንግስት የህክምና ተቋማት የመድኃኒት መደብሮች ላይ ለስኳር ህመም የሚሆን መድኃኒት እጥረት መኖሩን ተከትሎ ያቅርቦቱ ጉዳይ እንዴት ነው?
TRACK

ከሰሞኑ ባንዳንድ የመንግስት የህክምና ተቋማት የመድኃኒት መደብሮች ላይ ለስኳር ህመም የሚሆን መድኃኒት እጥረት መኖሩን ተከትሎ ያቅርቦቱ ጉዳይ እንዴት ነው?

00:00

ነሀሴ 1፣2016

በጤና ተቋማት ላይ የሚከሰት የመድሀኒት እጥረትን ተከትሎ ጥያቄው ዘወትር ወደ እኔ ቢመጣም የህክምና ተቋማት ያለባቸውን ውዝፍ የመድሀኒት እዳ በጊዜ ያለመክፈላቸው እና ፍላጎታቸውን አለማሳወቃቸው ለችግሩ ዋና ምክንያት ሆኗል ሲል የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ተናገረ።

ከሰሞኑ ባንዳንድ የመንግስት የህክምና ተቋማት የመድኃኒት መደብሮች ላይ ለስኳር ህመም የሚሆን መድኃኒት እጥረት መኖሩን ተከትሎ ያቅርቦቱ ጉዳይ እንዴት ነው? ስንል መድኃኒት አቅራቢውን ተቋም ጠይቀናል።

በመድሃኒት ግዥ በኩል በተለይ የስኳር መድሀኒት በበቂ ሁኔታ ግዥ ተፈጽሟል ያሉን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አወል ሀሰን ለመጪዎቹ 8 ወራት ድረስ የሚሆን ክምት እንዳለ ነግረውናል።

በመድኃኒት አቅርቦት ሥርዓት ውስጥ ብዙ ባለድርሻዎች አሉ የሚሉት አቶ አወል ነገር ግን የመድኃኒት እጥረት በተቋማት ላይ ሲከሰት ቅድሚያ የሚጠይቀው ይኸው ተቋም ቢሆንም የህክምና ተቋማት በዱቤ የወሰዱትን መድሃኒት ክፍያ በጊዜ ያለመፈፀም እና ፍላጎታቸውን ማሳወቅ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ለሚፈጠረው ጥረት ምክንያት ነው ብለዋል።

Comments

00:00