የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲመለስ የ850 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ፀድቆለታል ተባለ፡፡
TRACK

የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲመለስ የ850 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ፀድቆለታል ተባለ፡፡

Avatar

ግንቦት 14 2017

ለግንባታ ሚሊዮኖች ብር ከፈሰሰበት በኋላ ሥራ አቁሞ የተዘጋው የጣና በለስ የስኳር ፋብሪካ ወደ ምርት እንዲመለስ የ850 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ፀድቆለታል ተባለ፡፡

ፋብሪካው በ2,000 ሄክታር ቦታ ላይ የአገዳ ልማት እየተከናወነለት መሆኑን ሰምተናል፡፡

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ይህ ሁሉ ድጋፍ ከተደረገለት በኋላ በ2018 ዓ.ም ማገባደጃ ወይም 2019 መግቢያ ምርት ማምረት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሰምተናል።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የአየር ጠባዩ የሚስማማ ውሀውም የተንጣለ ቦታ በመሆኑ ሌሎች የሰብል ምርቶችን ለማምረት ወደ ስራ ተገብቷል ተብሏል።

የጣና በለስ ስኴር ፋብሪካ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በአመራር የተሻለ እንዲሆነእ በየደረጃው እየተደገፈ ነው ተብሏል።

ወሬውን የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር) ነግረውናል።

Comments

Avatar