በዘመን መለወጫ በዓል ወቅት ውሃ ከቧንቧ እንዳይጠፋ፣ መብራት ሄደ እንዳይባል ዝግጅት መደረጉን ተቋማቱ ተናገሩ
TRACK

በዘመን መለወጫ በዓል ወቅት ውሃ ከቧንቧ እንዳይጠፋ፣ መብራት ሄደ እንዳይባል ዝግጅት መደረጉን ተቋማቱ ተናገሩ

Avatar

ጳጉሜ 5 2017

በዘመን መለወጫ በዓል ወቅት ውሃ ከቧንቧ እንዳይጠፋ፣ መብራት ሄደ እንዳይባል ዝግጅት መደረጉን ተቋማቱ ተናገሩ፡፡

የድንገተኛ እና የእሳት አደጋዎች እንዳይከሰቱ፤ ከተከሰቱም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ሰምተናል፡፡

ለበዓል የኤሌክትሪክ መቆራረጥ እንዳይከሰት ዝግጅት አድርጌያው ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጡ ቢከሰትም በአፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጥ ቡድን ተቋቁሟል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ውሃ ፍሳሽ ባለስልጣንም ውሃ እንዳትጠፋ እየሰራሁ ነው ሲል አስረድቷል፡፡

Comments

Avatar