በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ላይ፤ ወጥ የሆነ ዋጋ እንዲኖረው ሊደረግ መሆኑ ተሰማ
TRACK

በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ላይ፤ ወጥ የሆነ ዋጋ እንዲኖረው ሊደረግ መሆኑ ተሰማ

Avatar

ሚያዝያ 14 2017

በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ላይ፤ ወጥ የሆነ ዋጋ እንዲኖረው ሊደረግ መሆኑ ተሰማ።

የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይትን በተመለከተ የዋጋ ወጥነት ባለመኖሩ በተለይ በበዓላት ወቅት በየመንገዱ እንዲወድቅ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል፣ የተባለለት ይህ አሰራር በቅርቡም ወደ ስራ እንደሚገባም የነገረን የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንደስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ነው።

በአምራች ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንደስትሪ ግብአት ዴስክ ሀላፊ አቶ ታረቀኝ ዲዳ ይሄ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ነጋዴዎች አላግባብ የሚጥሉትን ዋጋ እንዲቆጣጠር ያስችላል ብለዋል።

Comments

Avatar