የስራ ክህሎት እና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ነዋሪዎችን ለማሰልጠን ከ4,000 በላይ አሰልጣኞች ተሰማርተዋል ተባለ
TRACK

የስራ ክህሎት እና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ነዋሪዎችን ለማሰልጠን ከ4,000 በላይ አሰልጣኞች ተሰማርተዋል ተባለ

Avatar

መስከረም 7 2018

በየመንደሩ ቀጭቃጭ፣ ሸክላ ሰሪ እና ሌላም ሌላ እየተባሉ ቦታ የማይሰጣቸውና መሰል የተለያየ የስራ ክህሎት እና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ነዋሪዎችን ለማሰልጠን ከ4,000 በላይ አሰልጣኞች ተሰማርተዋል ተባለ፡፡

ይህም ሀገር በቀል የስራ ፈጠራዎች እና የጎጆ ኢንዱስትሪዎችን የተሻለ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡

ይህንን የነገሩን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢኖቬሽን እና ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኃላፊ የሆኑት ብርሃኑ አደሬ ናቸው፡፡

እነዚህ አሰልጣኞች እንዴት ነው ስራቸውን የሚከውኑት ብለን ለሀላፊው ላነሳነው ጥያቄ፤ አሰልጣኞቹ በተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ነባር የስራ ባህሎችን በመለየት ህብረተሰቡን በማወያየት እና ከነባሩ በተሻለ መልኩ አድጎ የገቢ ምንጭ እንዲሆኑ ሞያዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች የተለመዱ የስራ ባህልምና የሰው ሀብት እንዳለ የሚጠቅሱት ሀላፊው እነዚህን ሀብቶች በማዘመን እና ሳይንሳዊ በመሆኑ መንገዶች ማገዝ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

Comments

Avatar