3 የላዳ ታክሲ ማህበራት አዳዲስ መኪናዎች ተረከቡ
TRACK

3 የላዳ ታክሲ ማህበራት አዳዲስ መኪናዎች ተረከቡ

00:00

የካቲት 11፣2016

3 የላዳ ታክሲ ማህበራት አዳዲስ መኪናዎች ተረከቡ፡፡

ማህበራቱ አጠቃላይ 69 አባላት ያሏቸው ሲሆን መኪናውን ያቀረበላቸው አሚጎስ የቁጠባ እና ብድር ስራ ማህበር እንደሆነ ሰምተናል፡፡

ማህበራቱ አሮጌ የላዳ ታክሲዎቻቸውን በአዲስ መኪና የቀየሩት ከህብረት ስራ ማህበሩ በተመቻቸላቸው ብድር አማካኝነት ነው ተብሏል፡፡

አሚጎስ የቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር እንደተናገረው 3ቱ የላዳ ታክሲ ማህበራት አባሎቻቸው 20 ከመቶ እንዲቆጥቡ በማድረግ አዳዲስ መኪናዎች አስረክቤያለሁ ብሏል፡፡

የአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር የሽያጭ ክፍል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው በኃይሉ ለሸገር እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ላዳ ታክሲ ማህበራት አዳዲስ መኪኖችን አስረክቧል፡፡

ማህበሩ ለአባሎቹ ከዚህ በፊት ብድር ሲያቀርብ ከ1 እስከ 3 ወር ድረስ ያስፈልግ ነበር ያሉ ሲሆን አሁን አዳዲስ መኪኖች የወሰዱት 3 ማህበራት ግን በ20 ቀን ውስጥ አስፈላጊውን መስፈርት በሟሟላታቸው መኪናቸው ተረክበዋል ይላሉ፡፡

የማህበሩ አባል ሆነው ሲቆጥቡ የነበሩ ለነበሩ የላዳ ታክሲ ማህበራት ቁጠባ አዳዲስ መኪኖቻቸው እንዲረከቡ አድርጌያለሁ ያለው አሚጎስ ከዚህ በኋላም በማህበር ተደራጅተው ወደ አሚጎስ የሚመጡ የላዳ ታክሲ ማህበራት ተመሳሳይ አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ ብሏል፡፡

Comments

00:00