00:00
ጥቅምት 5 2018
በአዲስ አበባ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ምዝገባ ጥቅምት 1 መጀመሩና እስከ ህዳር 30 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተነገረ፡፡
ከማህበረሰብ ከሚሰበሰበው መዋጮ በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም ብቻ ለአገልግሎቱ 1.3 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ተብሏል፡፡
ጥቅምት 1 የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡
የቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ በ2017 ዓ.ም ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መጠቀማቸውን ተናግረው በዚህ አመትም በተለያየ ምክንያት አገልግሎቱን ያቋረጡትን ታሳቢ በማድረግ ከሁለት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ባሉ የመንግስት ጤና ተቋማት ተጠቃሚ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
Comments
00:00