ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቷን ቆጥራ የምታውቅበትና የምታስተዳድርበት ሀገራዊ የቱሪዝም ካርታ እያሰናዳች ነው።
TRACK

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቷን ቆጥራ የምታውቅበትና የምታስተዳድርበት ሀገራዊ የቱሪዝም ካርታ እያሰናዳች ነው።

Avatar

ግንቦት 26 2017

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብቷን ቆጥራ የምታውቅበትና የምታስተዳድርበት ሀገራዊ የቱሪዝም ካርታ እያሰናዳች ነው።

የቱሪዝም ሀብቷን በተመለከተ የት ምን አለ የሚለውን በማጥናትና በማወቅ ሀብቷን ለማስተዳደር ያስችላታል የተባለለት የቱሪዝም ሀብት ካርታ( #Resource_Mapping ) ስራ ከዓለም ባንክ ጋር በትብብር የሚሰራ ነው ተብሏል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ እንደነገሩን በቅድሚያ ስራው የተጀመረው የሲዳማ ክልል ሰነድ ተጠናቋል በቅርብ ጊዜ ውስጥም ይፋ ይደረጋል።

የቱሪዝም ሀብትን በዝርዝር ለማወቅ የሚያስችለው መረጃ መኖር በየትኛው ቦታ ላይ ምን ሀብት አለ፣ ምንስ መሰራት አለበት የሚለውን በሀገር አቀፍ ደረጃ ቀድሞ ለማወቅ ያስችላል።

ይህም የተበታተነውን አሰራር መልክ የሚያስይዝ፣ የቱሪዝም ልማት ስራውም ከሌላው ዘርፍ ጋር ተናቦ እንዲሄድ የሚያደርገው ነው ብለውናል።

Comments

Avatar