የካቲት 30፣2016
በቅርብ ጊዜ ስራው ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የካፒታል ገበያ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ኩባንያዎችን ለመደገፍ፣ መንገዱን ለማሳየት ሁለት ተቋማት የትብብር ስምምነት አደረጉ፡፡
ተቋማቱ ኤም ኤል ኤ(MLA) የተባለው የህግ ቢሮ እና አክሲስ ካፒታል(Axis Capital) ናቸው፡፡
ከ25 ዓመታት በላይ በፕሮጀክት ፋይናንስ እና በድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ በድርጅት እና ግብይት ህግ ስራ ልምድ አለኝ ያለው የምህረተ አብ ልዑል የህግ ቢሮ(ኤም ኤል ኤ) ከአክሲስ ካፒታል ጋር ያሰረው የትብብር ስምምነት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ስራ ቀና እንዲሆን ያግዛል ተብሏል፡፡
የትብብር ስምምነቱ ዋና ዓላማም ወደ ካፒታል ገበያው መግባት ለሚፈልጉ ኩባንያዎችን መንገዱን ማሳየት ነው ተብሏል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
#Ethiopia #ShegerWerewoch #ካፒታል_ገበያ #Axis_Capital #MLA #አክሲስ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments