TRACK
በአዲስ አበባ የመንግስት ወይንም 4 ቁጥር የለጠፋ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግ እየተላለፉ አስቸግረውኛል ሲል የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ተናገረ፡፡
ጥቅምት 19 2018
በአዲስ አበባ የመንግስት ወይንም 4 ቁጥር የለጠፋ ተሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግ እየተላለፉ አስቸግረውኛል ሲል የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ተናገረ፡፡
በሶስት ወር ውስጥም ከ270 በላይ የመንግስት ተሽከርካሪ ሾፌሮች መቀጣታቸውም ሰምተናል፡፡
ኮድ 4 መኪና አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግን በመጣስ፣ እንደፈለግን እንሁን ማለታቸው ትራፊክ ህግና ደንብን በማስከበር ስራውን በሚያከናወንበት ጊዜ እንቅፋት እንደሆኑበት ቢሮው አስረድቷል።
በአዲስ አበባ ትራፊክ ማነጅመንት የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያሌው ኢቴሳ ህግን ለማስከበር መነሻው ህግ ነው ፣ በህግ ፊት ደግሞ ሁሉም እኩል ነው ቢባልም አንዳንድ ባለስልጣናት ግን እንደፈለጉ ባልተፈቀደ መንገድ ያሽከረክራሉ፣ በተቃራኒ መንገድ ይነዳሉ ብለዋል፡፡
Comments