‘’75 በመቶው የተቋሙ ደንበኛ የ1፣ የ3 እና የ5 ብር ፓኬጅ የሚሞላ ነው’’ ኢትዮ ቴሌኮም
TRACK

‘’75 በመቶው የተቋሙ ደንበኛ የ1፣ የ3 እና የ5 ብር ፓኬጅ የሚሞላ ነው’’ ኢትዮ ቴሌኮም

00:00

ታህሳስ 23፣2017

ኢትዮ ቴሌኮም ተግባራዊ ያደረግሁት የታሪፍ ማሻሻያ 75 በመቶ ተጠቃሚዎችን የሚመለከት አይደለም አለ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ በፓርላማው ተገኝተው ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ 75 በመቶው የተቋሙ ደንበኛ የ1፣ የ3 እና የ5 ብር ፓኬጅ የሚሞላ ነው ብለዋል፡፡

የተጠቀሱትን የገንዘብ መጠን የሚጠቀሙት ላይም ምንም ዓይነት የታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም ብለዋል፡፡

ባለፉት 6 ዓመታት ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው በአነስተኛ ታሪፍ እንደነበር ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል፡፡

Comments

00:00