ህዳር 26፣2017
በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ችግር የሆነውን የህፃናት ሞትና መቀንጨርን ቀላል በሆነ መንገድ መከላከል ይቻላል ተባለ፡፡
በኢትዮጵያ በሕፃናት መቀንጨርና በተመጣጠነ ምግብ ዙሪያ የሚሰራው አለም አቀፉ ሚለርስ ፎር ኒውትሬሽን ኢኒሼቲቭ (Millers for Nutrition) የተባለው ተቋም በየአመቱ የሚሞቱና የሚቀነጭሩ ሕፃናትን ለመርዳት የስንዴና የዘይት ምርት በቀላሉ ማበልፀግ ይቻላል ሲል ለሸገር ሬዲዮ ተናግሯል፡፡
የሚለርስ ፎር ኒውትሬሽን ኢንሼቲቭ የኢትየጵያ ፕሮግራም ማናጀር አቶ ያዕቄም አምሳሉ ችግር ስላሉትና ስለ መፍትሄው ነግረውናል፡፡
በኢትዮጵያ 39 በመቶ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት የቀነጨሩ ናቸው፡፡
Comments