00:00
የካቲት 24 2017
በኢትዮጵያ ለትምህርት ሥርዓቱ መጓደል እና ጥራት ከሚነሱ ዋና ዋና ችግሮች መካከል የመምህራን የብቃት ማነስ አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡
ወደ ዘርፉ ፈልጎ የሚገባ የሰው ሀይል ቁጥር ጥቂት መሆኑ፣ ብቁ የሚያደርጋቸውን የትምህርት ዝግጅት እና ስልጠና አለማግኘታቸውም እንደ መንስኤ ይነሳል፡፡
በተለይ ደግሞ ወደ ገጠሪቱ የሀገሪቱ አካባቢ ያሉ የትምህርት ተቋማት ላይ የሚመደቡ መመህራን ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ይላሉ የትምህርት ባለሙያዎች፡፡
የትምህርት ጥራት መውደቅ፣ የመምህራን ብቃት ማነስ ነው ለዚህ ደግሞ መምህራንን በስልጠና ማገዝ እና ወደ ዘርፉ ሲገቡ ብቃታቸውን መመዘን የጠበቅብናል የሚለው ዘርፉ ላይ የተለያዩ ስራዎችን የሚከውነው ቅን ልቦና ብሩህ ተስፋ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አሁን እየታየ ያለው ግን በተለይ ደግሞ ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ እና የገጠር ከተሞች ላይ ችግሩ ከፍተኛ መሆኑን አስተውያለሁ ብሏል፡፡
ብቁ መምህራን እጥረት መኖሩን በማየቴ ከ2016 ክረምት ጀምሮ መምህራን የአቅም ማሻሻያ እንዲወስዱ አደርጋለሁ በሚል ትምህርት ሚኒስቴር ስራዎችን ሲከውን ቆይቷል፡፡
Comments
00:00