ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ
TRACK

ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ

Avatar

ጥቅምት 19 2018

ከአንዱ ባንክ ወደ ሌላኛው ባንክ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ በአንደኛው ባንክ ካርድ በሁሉም መጠቀም የሚያስችል ስርዓት የዘረጋው #ኢትስዊች ባለፈው በጀት ዓመት ከግብር በፊት 1.42 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ተናገረ።

ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ34 በመቶ ብልጫ እንዳለው የኢትስዊች የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳሲ አቶ ሰለሞን ደስታ ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ የ1,000 ብር አክሲዮን የትርፍ ድርሻ 486.4 ብር ደርሷል ተብሏል።

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ በአጠቃይ 2.2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱንም ይህም ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 በመቶ ጭማሪ እንዳለው የቦርድ ሰብሳቢው ጠቅሰዋል።

Comments

Avatar