ነሐሴ 9፣2016
አስመጪዎች በጉሙሩክ ኮሚሽን ክፈሉ የተባሉት ቀረጥ ጉዳይ እያወዛገበ ነው፡፡
አስመጪዎቹ የቀድሞ ህግ በደብዳቤ ተሸሮ ያለአግባብ ከእጥፍ በላይ ቀረጥ እንድንከፍል ተጠይቀናል እያሉ ነው፡፡
መነሻው ከውጪምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
በዚህም የስድትስና የስምንት ሚሊዮን ብር ጭማሪ መክፈል አንችልም፤ ይህንን ባለመክፈላችን ደግሞ እቃችን ይወረስብናል የሚል የግል ስጋታቸውእና ቅሬታቸውን ለሸገር ተናግረዋል፡፡
ቀደም ብሎ በነበረው ህግ አስመጪዎች ቀረጥ መክፈል የነበረባቸው እቃ ያስመጡበትን ሰነድ ባስመዘገቡበት ቀን ነበረ፡፡
Comments