የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማን ማቋቋሙ ትልቅ ውሳኔ እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ
TRACK

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማን ማቋቋሙ ትልቅ ውሳኔ እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ

00:00

የካቲት 12፣2016

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ ምዕራብ አካባቢዎች ለመከወን ያቀዳቸው ሠፋፊ የልማት ፕሮጀክቶች በ’’ሸኔ ታጣቂዎች’’ ምክንያት ከፍተኛ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

ሸገር ከተማን ማቋቋማችን ትልቁ እና ጠቃሚው ውሳኔያችን ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በአዳማ በተካሄደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት(ጨፌ ኦሮሚያ) ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማን ማቋቋሙ ትልቅ ውሳኔ እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

የከተማው መመስረት ባልተገባ መንገድ በግለሰቦች የሚያዝ የህዝብ እና የመንግስት መሬት እንዳይኖር ለመከላከል ያግዛል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በአዳማ በተካሄው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በሚታየው የሠላም ችግር ዙሪያም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተለይም በሸኔ ታጣቂዎች ምክንያት የሰዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እየተስተጓጎለ ነው፤ የልማት ስራዎችም ቆመዋል በሚል ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

በተለይ የኦሮሚያ ምዕራብ አካባቢ ነዋሪዎች በ’’ሸኔ ታጣቂዎች’’ ምክንያት ልማት እንደተስተጓጎለባቸው የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ያቀድነው ግን ክልሉ ከተመሰረተ አንስቶ ተከናውኖ የማያወቅ የልማት ስራ ነበር ሲሉ አክለዋል።

።

ንጋቱ ረጋሳ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ጨፌ_ኦሮሚያ #ኦሮሚያ_ክልል #ሰላም

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

00:00