የጉራጌ ዞን በዘንድሮው የመስቀል በዓል ከ800,000 በላይ ጎብኚዎችን ለመቀበል ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ
TRACK

የጉራጌ ዞን በዘንድሮው የመስቀል በዓል ከ800,000 በላይ ጎብኚዎችን ለመቀበል ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ

00:00

መስከረም 14፣2017

የመስቀል በዓል በሰፊው የሚከበርበት የጉራጌ ዞን በዘንድሮው በዓል ከ800,000 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎችን ለመቀበል ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ፡፡

የ2017 እቅድ ከአምናው ጋር ሲነፃፅርም የ40 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተነግሯል፡፡

ይህንን የተናገረው የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ነው፡፡

ዞኑ መስቀልን አስታኮ የሚያዘጋጀው ፌስቲቫል መኖሩም የተነገረ ሲሆን ለሰባተኛ ጊዜ ከመስከረም 11 ቀን ጀምሮ እንዳሰናዳ ተናግሯል፡፡

ከዓመት ዓመት በዞኑ ያለው የቱሪዝም ፍሰት እየተስተካከል እና እየጨመረ መምጣቱን ሰምተናል፡፡

Comments

00:00