00:00
ግንቦት 27፣2016
በአዲስ አበባ ከተማ፤ የአየር ብክለት መጠን ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ጥናት አሳየ።
ከአለም አቀፍ እና ከሀገር ውስጥ አየር ብክለት ስታንዳርድ መለኪያ አንጻር ሶስት እና አራት እጥፍ መጨመሩም ተነግሯል።
በከተማዋ ከፍተኛ የአየር ብክለት መጠን የተፈጠረው በተለይ በተሽከርካሪ ጭስ፣ ከማገዶ ወይም ከከሰል እንዲሁም አግባብ ባልሆነ የቆሻሻ አወጋገድ የመጣ መሆኑም በጥናት ተመላክቷል።
በከተማዋ አሁን ያለው የአየር ብክለትም ከፍተኛ ስጋት ከመሆን ደረጃ ላይ መድረሱም ተነግሯል።
አሁን ያለው የአየር ብክለት መጠንም ከአለም አቀፍ የአየር ብክለት መለኪያም ባለፈ ከሀገር ውስጥ መለኪያም አልፎ 25% ጨምሯል ተብሏል።
በዚህም በህብረተሰብ ጤና ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑም ተነግሯል
ፍቅሩ አምባቸው
Comments
00:00