ሐምሌ 8፣ 2016
በኢትዮጵያ ስራ መፍጠር፣ ቢዝነስ መጀመር መሰናክል ማነቆው ብዙ ነው።
የስራ ቦታ እጦት፣ ስራ መጀመሪያ ወረት አለማግኘት፣ ንግድ ፍቃድ ለማውጣት ያለው ቢውሮክራሲ እና ውጣ ውረድ ከችግሮቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
እነዚህን ችግሮች ተቋቁመው ለእነሱም ሆነ ለሌሎች እንጀራ የፈጠሩ ቁጥራቸው ጥቂትም ቢሆነ አሉ።
ኬብሮን ግዛቸው እና እስክንድ ብርሃኑ ከእነዚህ መከካል የሚመደቡ ናቸው።
ኬብሮን ግዛቸውና ጓደኞቿ የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ማሽን እንኩቤይተር ሰርተዋል፡፡
‘’ከዚህ በፊት የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩት ለማግኘት እረጅም ቀናትን መጠበቅ ግዴታ ነበር’’ ያለችው ኬብሮን ለዚህም ምክንያቱ ከውጪ ሀገር የሚገባው ማሽን ዋጋ መወደድ እና በአቅራቢያ አለመገኘቱ ነው ብላለች፡፡
Comments