የአካል ጉዳት ለገጠማቸው ህፃናት ላለፉት 16 ዓመታት የአጥንት ቀዶ ጥገና ሲያደረግ የቆየው ‘’ኪዩር የልጆች ሆስፒታል’’ በማስፋፊያ ስራ ላይ መሆኑ ተሰማ
TRACK

የአካል ጉዳት ለገጠማቸው ህፃናት ላለፉት 16 ዓመታት የአጥንት ቀዶ ጥገና ሲያደረግ የቆየው ‘’ኪዩር የልጆች ሆስፒታል’’ በማስፋፊያ ስራ ላይ መሆኑ ተሰማ

00:00

ነሐሴ 15፣2016

በተፈጥሮ እና በልዩ ልዩ መንገዶች የአካል ጉዳት ለገጠማቸው ህፃናት ላለፉት 16 ዓመታት የአጥንት ቀዶ ጥገና ሲያደረግ የቆየው ‘’ኪዩር የልጆች ሆስፒታል’’ በማስፋፊያ ስራ ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡

መሰረቱን አሜሪካን ሀገር ያደረገው ‘’ራስ ጆንስ ፋውንዴሽን’’ በአዲስ አበባ ሐምሌ 19 መናፈሻ ጀልባ ባዘጋጀው የልጆች ሆስፒታል የሚሰጠውን የቀዶ ህክምና የአካል ማጠንከሪያ ስራው ለማስፋፋት የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡን የነገሩን የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬክተር አደይ አባተ ናቸው፡፡

ኪዩር ባለፉት ዓመታት በሰጠው አገልግሎት ከ35,000 ለሚበልጡ ህፃናት የአጥንት ቀዶ ጥገና ማድረጉ ታውቋል፡፡

ሙሉ በሙሉ ከአጥንት ቀዶ ጥገና ህክምና በተጨማሪ ልዩ ልዩ መድሐኒቶችን ጨምሮ ለታካሚ ልጆች ወላጆች የሚሰጠው አገልግሎት በነፃ መሆኑን ሰምተናል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

Comments

00:00