ዋሻ ውስጥ እያሉ አፈር የተናደባቸው የኦፓል ማዕድን አውጭዎች እስካሁን አልተገኙም ተባለ
TRACK

ዋሻ ውስጥ እያሉ አፈር የተናደባቸው የኦፓል ማዕድን አውጭዎች እስካሁን አልተገኙም ተባለ

Avatar

የካቲት 7፣2016

በደቡብ ወሎ ዞን በዋሻ ውስጥ እያሉ አፈር የተናደባቸው የኦፓል ማዕድን አውጭዎች እስካሁን አልተገኙም ተባለ፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በተለምዶ ‘’ቆቅ ውሃ’’ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ወጣቶች የኦፓል ማዕድን እያወጡ በነበረበት ወቅት ነው ዋሻው እንደተናደባቸው የተነገረው፡፡

ወጣቶቹን ለማውጣትም የቦታው አቀማመጥ ለማሽን የተመቸ ባለመሆኑ በሰው ኃይል በቁፋሮ ህይወታቸውን ለማትረፍ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ካለ ምንም መፍትሄ ስድስት ቀናትን እንዳስቆጠሩ የደላንታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያሌው በሪሁን ለሸገር ተናግረዋል።

ይህ መሳዩ ችግር በዞኑ ሲከሰት የመጀመሪያ እንዳልሆነ የተናገሩት አቶ አያሌው ቁጥራቸው በውል ባይታወቅም ከስምንት እስከ አስር የሚሆኑ ሰዎች የአደጋው ሰለባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገምቷል ብለዋል፡፡

የነፍስ አድን ስራው ችግሩ ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እየተሰራ ቢሆንም ተስፋ የሚሰጥ ነገር ግን እየታየ አለመሆኑን ሸገር ከወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ሰምቷል፡፡

ዋና አስተዳዳሪ የኦፓል ማዕድን አውጭዎቹ በምን ያህል እርቀት ውስጥ ተቀብረው እንዳሉ በውል አይታቅም፣ የነፍስ አድን ስራውን የሚከውኑ ሰዎች ግን እስከ 70 ሜትር ድረስ መቆፈራቸውን ተናግረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ተስፋ የሚሰጥ ነገር እንዳለታየ ነው የሰማነው፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #���ዋሻ_መናድ #ደላንታ_ወረዳ #የኦፓል_ማዕድን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Comments

Avatar