አጠቃላይ ህጎችና አሰራሮች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በጉትጎታ ላይ ነው
TRACK

አጠቃላይ ህጎችና አሰራሮች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በጉትጎታ ላይ ነው

Avatar

ታህሳስ 24፣2017

የኢትዮጵያ መንግስት የሚያወጣቸውን አጠቃላይ ህጎችና አሰራሮች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በጉትጎታ ላይ ነው፡፡

የህገ መንግስት መሻሻያ እንዲደረግም ማህበሩ ጠይቋል ተብሏል፡፡

ከተመሰረተ አምስት ዓመታት የሞሉት የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያ አካል ጉዳተኛ ማህበር በሰላሙ ሀገሪቱ አካል ጉዳተኛውን ታሳቢ በማድረግ እና መብቱንም እንዲጠበቅለት እየሰራ መሆኑን ለሸገር የነገሩት የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ጥላሁን ናቸው፡፡

በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ የህገ መንግስት መሻሻል ጉዳይን አቅርበናል ያሉት ዳይሬክተሩ እንደ ጎረቤት ሀገራት በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አካል ጉዳተኛውን የሚወክል ቋሚ መቀመጫ እንዲኖር እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

በዓመት ውስጥ በህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት በሚደረጉ ውይይቶች ስለ አካል ጉዳተኞች ጉዳይ ሲነሳ አልሰማም የዚህ ምክንያት ደግሞ አካል ጉዳተኛውን የሚወክል እና ህመሙ የሚሰማው ሰው ባለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡

የኔነህ ሲሳይ

Comments

Avatar