መስከረም 6፣2017
በተያዘው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የውጪ አልሚዎች በአይሲቲ(ICT) የስራ መስክ ኢንዲሳተፉ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ አይሲቲ ፓርክ ተናገረ፡፡
አሁን ባለው የICT ፓርክ ህንፃ ሁሉም ቦታዎች በሀገር ውስጥ አልሚዎች ተይዘዋል ያሉት የፓርኩ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሄኖክ አህመድ ናቸው፡፡
ስራ አስኪያጁ በገባው አዲስ ዓመት ለውጪ አልሚዎች የሚሆኑ የስራ ቦታዎችን እናሰናዳለን ብለዋል፡፡
በዚህም የውጪ አልሚዎች በICT መስክ እንዲሳተፉ ይደረጋል ሲሉ አቶ ሄኖክ ነግረውናል፡፡
Comments